ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
82

የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2.የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 3. ፣የውጭ ፈርኒቸር ዕቃ፣ ሎት 4. የመኪና ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ/ ብር በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
  2. ተጫራቾች ሎት የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 3. የውጭ ፈርኒቸር ዕቃ ፣ሎት 4. የመኪና ጎማ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ ፡፡ የዞኑ አድራሻ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገ/ውሃ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቢሮ ሶስተኛ ፎቅ ነው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደርሰኝ መሂ1 በተቆጠረ በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የጠቅላላ ግዥውን ዋጋ5 በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ የግዢውን ዋጋ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ ማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስረከቢያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡የጨረታ ሰነዱን 100 /አንድ መቶ/ ብር ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የመጫረቻ ሰነዱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታውን ለመገምገም በርካታ ጊዜ ለማይወስዱና ውስብስብ ላልሆኑ ግዥዎች ከአርባ (40) ቀናት መብለጥ እንደሌለበት እያወቁ የመጫረቻ ሰነዱን መሙላት አለብዎት።
  5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኃላ በተጨማሪ ውል እስኪቋረጥ ድረስ ለሚቆይ ሃያ (20) ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምዕራብ ጎንደር ዞንፖሊስ መምሪያ ግዥና ፋይናስ ቡድን መሪ ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘወተወር በስራ ሰዓት 24/06/2017ዓ/ም እስከ የመጋቢት 08/07/2017ዓ/ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ15 ቀን የአየር ላይ ቆይታ በ09/07/2017 ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ምዕ/ጎ/ዞ/ ፖሊስ መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ግቢ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልፅ ይከፈታል ፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ድምር ስለሆነ የሙሉ እቃ ዋጋ መሙላት አለበት ካልተሟላ ግን ከጨረታ ወጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
  9. በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ ዋጋ እና የሞዴል መረጃን እንዲሁም የማይነበብ ስርዝ ድልዝ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 331 05 94/091 823 70 63/091 85 81 034 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. ግዥ ፈፃሚ አካል የጨረታውን አሸናፊ በሚመርጥበት ጊዜ መለኪያው ተለይቶ የሚታወቅ እስከሆነ ድረስ በእያንዳንዱ የእቃ መለኪያ የተሰጠውን የነጠላ ዋጋ ወይም ሌሎች የውል ቃሎችና ሁኔታዎችን ሳይለወጡ የዕቃውን ብዛት ወይም መጠን እሰከ 20 በመቶሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
  13. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የሞላወን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት ወይም ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ በምዕ/ጎ/ዞ/ዐቃቢ ህግ መምሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት ፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ሆኖም የምክንያቶቹን አግባብነት እንዲያስረዳ አይገደድም፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here