ቁጥር ግጨ 06/2017
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የተለያዩ የፋይናንስ ህትመቶችን|ገንዘብና ልማት መጸሄት|የፅዳት እቃዎችን|የመኪና ጎማዎችን| የፕሪንተር ቀለም እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል፤የእቃው/የአገግሎቱ ግዥ መጠን በኢትዮጵያ ብር ከ200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዞው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (ለአስራ ምስት) ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ አንደኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 01 ወይም 02 በአካል በመቅረብ የማይመለስ የኢትዩጵያ ብር00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አንድኛ ፎቅ ላይ የገዙትን የመጫረቻ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፓስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ከተማ በሚገኝው አብክመ ገንዘብ ቢሮ 6ኛ ፎቅ ላይ ከትልቁ አዳራሽ ላይ ይከፈታል፡፡
- በመሆኑም በዕለቱ ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅቶች ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን በ16ኛው (በአስራ ስድስተ ኛው) ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለተወዳደሩባቸው እቃዎች ወይም አገልግሎቶች የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን ለሎት1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎ ብር 1500/አንድ ሽህ አምስት መቶ/፣ 2.ለሎት2 ብር 6000/ስድስት ሽህ/፣ 3.ለሎት4 ብር 2000/ሁለት ሽህ/፣ 4.ለሎት9 ብር 10000/አስር ሽህ/፣ለሎት10ብር 50000/አምሳ ሽህ/፣ ለሎት13ብር15000/አስራ አምስት ሽህ/ በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፓስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ውድድሩ የተጫራቾችን መመዘኛ መስፈርቶችን ከአሟሉት ተጫራች ድርጅቶች መካከል በእያንዳንዱ እቃ ወይም አገልግሎት ግዥ ላይ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት አሸናፊ ሁኖ ይመረጣል*
- የሚገዙ የእቃ ወይም አገልግሎት ግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን)፤መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 0582201356 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይቻላል፡፡
የአብክመ ገንዘብ ቢሮ