የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽዳት እቃዎች እና የተሸከርካሪ መኪና ዕቃ / የእሪቮ መኪና ኬሪ ቦይ፣የእሪቮ መኪና ፉል ሴት ፣የእሪቮ መኪና ዊንድ ሸድ/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡፡ 1ኛ. ሎት 1 የጽዳት እቃዎች ፣ 2ኛ. ሎት 2 የተሸከርካሪ መኪና ዕቃዎች/የእሪቮ መኪና ኬሪ ቦይ፣የእሪቮ መኪና ፉል ሴት፣የእሪቮ መኪና ዊንድ ሸድ/
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/የሚያቀርብ፡፡
- ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ / ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ለእያንዳንዱ ሎት እቃ ብር 60,000/ስልሳ ሽህ/ብቻ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ አብክመ ጤና ቢሮ ግዥ ፋይ/ ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥ ክፍል/ጃይካ ህንፃ ጨረታው በወጣ በ16ኛዉ ቀን በ 8:30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ቢሮው የግዥዉን መጠን እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለያንዳንዱ ሰነድ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈውን የጽዳት እቃዎች እና የመኪና ዕቃ ቢሮ ድረስ አቅርቦና ገጣጥሞ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታዉ መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ቁጥር – ጃይካ ህንፃ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582221127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
አብክመ ጤና ቢሮ