ቁጥር 07/2017
በምስ/ጎ/ዞን የሞጣ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን በRoad Fund በጀት የሞጣ ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ለሚያሰራዉ የጠጠር መንገድ ጥገና package no AMHARA-MOTTA-CIP-MAT-02/2024/2025 ሎት1∙ ከበላይ አደራዉ ቤት እስከ ሙሉቀን ጌታሁን ቤት ድረስ ፣ ስፋቱ 2992 m² በGC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ካላቸዉ ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ።
- የግዥዉ መጠን ከብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ የጨረታዉን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸዉን ወቅታዊ የሆነና ለጽ/ቤት በአድራሻ የተፃፈ ማስረጃ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) ከፍለዉ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ በጥቃቅን የተደራጁ ወጣቶች ከአዳራጃቸዉ መ/ቤት ወቅታዊ የሆነና ለጽ/ቤት በአድራሻ የተፃፈ ደብዳቤ በመያዝ የጨረታ ሰነድ በነፃ ከሞጣ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 መዉሰድ ይችላሉ፡፡የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ወይም ለመዉሰድ ሲመጡ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ አድርጋችሁ ማምጣት አለባችሁ፡፡
- አሸናፊዉ ተጫራች የስራዉን የግል ተቋራጭ ከሆነ 15በመቶ፣የመንግስት የልማት ድርጅት ከሆነ ደግሞ 20ሪበመቶ በጥቃቅን ለተደራጁ ወጣቶች አዉት ሶርስ ወይም ሰብ ኮንትራት መስጠት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሎት 1 ∙ ለጠጠር መንገድ ጥገና ብር 10,000.00 (አስር ሽህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታዉ ላይ የሚወዳደሩበትን የግንባታ አይነትና ሎት በመፃፍ ከሞጣ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 ለጨረታ ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት ሁኖ በ31ኛዉ ቀን እስከ ጧቱ 4፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በ31ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡20 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም ባይገኙም በሞጣ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር ሁኔታ በስልክ ቁጥር 0586610221/1890 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 18 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና በተሻሻለዉ የግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጫራታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የሞጣ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን