የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለቻግኒ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚውል የተለያዩ እቃዎች ማለትም ሎት 1 ቋሚ አላቂ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች፤ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፤ ሎት 3 የመብራት እቃዎች ፤ ሎት4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ሎት 5 የእስፖርት እቃወች እና አልባሳት እና ሎት 6 የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- የግዥው መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 250/ሁለት መቶ/ በመክፈል ከቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ በመግዛት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት 1∙ ቋሚ አላቂ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች 10,000/አስር ሽህ/ ብር ፣ ሎት 2∙ የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች 25,000/ሃያ አምስት ሽህ/ ብር ፣ ሎት 3∙ የመብራት እቃወች 5,000.00/አምስት ሽህ ብር/ ፣ ሎት 4∙ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 10,000/አስር ሽህ ብር /፣ ሎት 5∙ የስፖርት እቃወች አልባሳት 10,000/አስር ሽህ ብር/ እና ሎት 6∙ የጽዳት እቃዎችን 15,000/አስራ አምስት ሽህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ /መሂ-1 /ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊ ተለይቶ ውል ከተያዘ በኃላ በራሱ ወጭ እስከ ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጥኃቱ 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል ፡፡
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ አድርጎ መመለስ አለበት፡፡
- ተጫራቶች ለግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት በተሞላው ጥቅል ድምር ዋጋ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582251721/0582251631 በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡
ቻግኒ ከ/አ/ገ/ ጽ/ቤት