ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
114

የግዥ መለያ ቁጥር አ/ማ/03/2017

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ኮሚሽን በጦርነቱ ለተጎዱ የመንግስት ተቋማት እና ለዲጅታል አይዜሽን  አገልግሎሉ የሚዉል የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች ማለትም እንደ ኮምፒተር ፡ ፕሪንተር ፡እስካነር እና የመሳሰሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፣
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይበተ.ቁ. 1- 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እቃዎች የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል  ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት  ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት መግዛትይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በ16ኛዉ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ቴክኒካል ግምገማ ለሚያስፈልጋቸዉ ዕቃዎች  የመጫረጫቻ ሰነዱን በትክክል ከሞሉ በኋላ ቴክኒካሉን እና ፋይናሻሉን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን እና ሰአት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582220580 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582209644/0582209646 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ኮሚሽን

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here