የገጠር ኮሪደር ልማት ተግባራዊ ሊደረግ ነዉ

0
186

በአማራ ክልል የኮሪደር ልማት በገጠሩ በሁሉም አካባቢዎች ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በገጠር ኮሪደር ልማት ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ ይዘትና የአተገባበር ስልቶችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዶክተር ድረስ በማብራሪያቸውም በሀገር ደረጃ እየተተገበረ ያለው የኮሪደር ልማት የሕብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ የሚቀይር፣ የተቀናጀ የመሠረተ ልማትን የሚያሟላ፣ የትራንስፖርት ፍስትን የሚያሳልጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድልን የሚፈጥር እና ሌሎችንም ዓላማዎች ይዞ እየተተገበረ መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ሰው ተኮር መሆኑን በማንሳት ልማቱን በገጠር በሁሉም አካባቢዎች ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል።
ይህም በተደራጀ መንገድ መሠረተ ልማቶችን ለአርሶ አደሩ ከማቅረብ ባሻገር የግብርና ሽግግር ሥርዓትን የሚያረጋግጥ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
እንደ ዶክተር ድረስ ማብራያ የገጠር ኮሪደር ልማት በርካታ መሠረት ልማቶችን የያዘ፣ የግብርና ልማት ተቀናጅቶ የሚፈፀምበት፣ ትምህርት፣ ከህሎትና ስልጠና የሚሰጥበት፣ ጤና እና ስነ ምግብን የያዘ፤ የማሕበረሰብ ልማት የሚካሄድበት፣ የአካባቢ ዘላቂነት፣ ዲጅታላይዜሽንና የፋይናንስ አካታችነት፣ የአለባበስና የአመጋገብ ሥርዓት፣ የባሕል እና የመዝናኛ ልማት ዋነኞቹ የመርሃ ግብሩ አንኳር ይዘቶች ናቸው።
የገጠር ኮሪደር ልማት አተገባበር ስልት በቅድሚያ በፓይለት ደረጃ በተመረጡ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ተግባራዊ በማድረግ በሂደትም የእነዚህን ልምድና ተሞክሮ በመውሰድ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተግባራዊ ይደረጋል ትብሏል።
መረጃው የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here