የደብረ ማርቆስ አጠ/ስፔ/ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ለኔትወርክ ኢንስታሌሽን የሚያስፈልጉ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ቢድ ቦንድ / ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000 /ሶስት ሽህ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ / ሲፒኦ/ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኞችን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ 15 ቀን ቆይቶ በ16 ተኛው ቀን ይከፈታል ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል ፡፡
- የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ /ብር በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን አንስቶ የሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን ለ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ ን/አ/ደ/የስ/ሂደት በአካል በመገኘት / በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል