የአምበሳሜ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ፅ/ቤት ትራንስፎርመር ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር tin ማቅረብ የሚችሉ ።
- ግዡ ከብር 200¸000/ሁለት መቶ ሽህ ብር / በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከ 1-4 ከተዘረዘሩት ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማኅተም ሊኖር ይገባል።
- የሥራውን እና የማሽኑን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም /ስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለሰ00 ብር በመክፈል አንበሳሜ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቀጥር 03 በመቅረብ መግዛ።ት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የስራና የማሽን አይነት 140,000/አንድ መቶ አርባ ሽህ/ ብር በባንክ ከተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፅ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው።
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናሉን በማሽግ ከፖስታው ጀርባ አንበሳሜ ከተማ ው/ፍ/አ/ፅ/ቤት በማለት ስምና የሚወዳደሩበትን አይነት በመግለፅ ዘወትር በስራ ሰአት በጨረታ ሳጥኑ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታው ሳጥን ከቀኑ00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸውን ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል 16 ኛዉ ቀን በአል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሎትም ሆነ በተናጠል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነው
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ድርጅት የማጓጓዣውን ሙሉ ወጪ ሸፍኖ ለተቋሙ የሚያስረክብ ይሆናል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝረዝር ሁኔታ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582580251/ 0923337620 ወይም ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ ።
የአምበሳሜ ከተማ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ፅ/ቤት