በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በUNDP በጀት ለጃናሞራ ወ/ት/ት ጽ/ቤት ለተማሪዎች ለመማሪያና ማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ ሎት1.ኮንባይን ዲስክ የተማሪዎች ወንበር፣ ሎት2.ጥቁር ሰሌዳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው ፡፡
- የቲን ነምበር ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው ፡፡
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1–4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በእያንዳንዱ ሎት የዕቃወቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1.5 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ጀምሮ በአየር ላይ ከ 08/07/2017 ዓ/ም እስከ 22/07/2017 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከ08/07/2017 እስከ-22/07/2017 ድርስ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 23/07/2017 ዓ/ም 8፡15 ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው ፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ-ብርሃን ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው የሚያስረክቡ ሲሆን ትራስፖርትን እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 0582940023/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት