የጨረታ ቁጥር
EEU/DMR/SC-PGS /NCB-10/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅን ለሪጅኑ እና በሥሩ ለሚገኙ አገ/መ/ማዕከላት አገልግሎት የሚሆን ወረቀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የዕቃ ዓይነት | ሎት | ብዛት | የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) | ጨረታዉ የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት
ቀን
|
1 | A4 ወረቀት | 01 | 2,000 | 25,000 (ሀያ አምስት ሺህ ብር) ብቻ፡፡ | መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ፣የአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ያላቸው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግስጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅን ቀበሌ 02 እንቦሳ የገበያ ማዕከል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በካሽ በመከፈል ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታው ሰነድ መውስድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስከበሪያ በሎት 25,000 (ሀያ አምስት ሺህ ብር) ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት አስከ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም 8፡00 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን መጋቢት 18/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም በደብረ ማርቆስ ቀበሌ 02 እንቦሳ የገበያ ማዕከል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የሪጅኑ ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (+251 581 78 46 33) መደወል ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅን