በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
85

የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት ሚዉሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2 የፋብሪካ ማቴሪያል እና ሎት 3 የመኪና ጎማ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸዉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና 2017 ዓ.ም የሥራ ግብር ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ያጠናቀቀ መሆን ይኖርበታል፡፡ (የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ) የሚችሉ፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ብር አንድ በመቶ የጨረታ ሳጥኑን ከመከፈቱ ቀድሞ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ያሸነፉትን የእቃ ዋጋ አስር በመቶ ወድያዉኑ /በሲፒኦ/ ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ዉል በመዉሰድ የተጠየቀዉን እቃ ጥራት ጠብቆ በኦሪጅናል ሊያቀርብ ይገባል፡፡
  4. ያሸነፉበትን እቃ ለማቅረብ ዉል የማይወሰድ ወይም ዉል ከወሰደ በኋላ እቃዉን የማያቀርብ ተጫራች ቢያጋጥም መ/ቤቱ ለዉል ማስከበሪያ የያዘዉን ሲፒኦ ጥሬ ገንዘብ መዉረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ 1 ዓመት ለሚደረስ ጊዜ በጨረታ እንዳይሳተፍ የማገድ ስልጣኑን ለመጠቀም ይገደዳል፡፡
  5. ማንኛዉም ተጫራች የማወዳደሪያ ዋጋ ሲሞላ ሁለት ኦርጅናል በሁለት ፓስታ ታሽጎ ማስገባት ከጨረታዉ እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ሳጥኑ መግባት ያለበት ኦርጅልናል እና ኮፒ ሆኖ በሁለት ፖስታ ታሺጎ ከፖስታዉ ላይ ኦርጅናል ኮፒ ተብሎ ተጽፎ ከሳጥኑ ዉስጥ ሊገባ ይችላል፡፡
  6. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛዉም ተጫራች የንግድ ፈቃዱን የማይመለስ 1 ኮፒ የግብር ከፋይ ምዝገባ 1 ኮፒ ፣ቫት (ቲኦቲ) የምስክር ወረቀት የማይመለስ 1 ኮፒ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች ለሚያቀርበዉ እቃ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ሊኖረዉ ይገባል፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ታስቦ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ የመ/ሰ/ከ/ገ//ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 210 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይቻላል፡፡
  10. ጨረታዉ በዚያው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሲሆን ታሽጎ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸዉ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. የሚቀርበዉን እቃ በተጠየቀዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  12. የሚቀርበዉ እቃ በኦሪጅናል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  13. በጨረታዉ ያሸነፈዉ ግለሰብ የሚያቀረበዉን እቃ ጽ/ቤቱ ድረስ የሚያመጣዉ በራሱ ወጭ መሆኑ ይታወቅ፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here