ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
85

የደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 2 የወለል ምንጣፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች በዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. በሎት ከጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ አንድ መቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ደ/ጐን/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 በመቅረብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በፖስታ ውስጥ አሽጐ ማቅረብ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፣ ገንዘቡም ቢጠፋ መ/ቤቱ ሊጠየቅ አይችልም፡፡
  7. መ/ቤቱ ለመግዛት የሚፈልገውን እቃዎች አይነት ዝርዝር የያዘ ሠነድ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 35 በመምጣት እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 35 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዩች ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛዉ ቀን 2፡30 ቢሮ ቁጥር 35 ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠዉ ወይም የሚለዩት በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ ነዉ፡፡
  11. አሽናፊው ድርጅት የአሸናፈዉን እቃ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ አለበት፡፡
  12. ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ኦሪጅናል እና ኮፒ ፈቃድ በመያዝ ሰነዱን በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸዉ አማካኝነት ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 03 86 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here