የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
102

የደብረ ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ 45 እና ለድርጅት3 አገልግሎት በድምሩ 48 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ።

  1. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ከ15/07/2017 እስከ 26/07/2017 ዓ/ም ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ስለዚህ መጫረት የምትፈልጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት እና በመመዝገብ የማይመለስ ብር00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከ15/07/2017 እስከ 26/07/2017 ዓ/ም ድረስ ባሉት 10 የስራ ቀናት በመንግስት የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 02 ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ26/07/2017 ዓ/ም በ 11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው 27/07/2017 ዓ/ም በ 3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ

ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ ነው፡፡

ሁሉም ተጫራቾች በፖስታ አሽገው ማስገባት ያለባቸው።

  1. የሀሳብና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ።
  2. በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ለድርጅት 15በመቶ እና ለመኖሪያ 20በመቶ የተከፈለበት።
  3. ኦርጅናል / ዋናውን/ ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ ናቸው፡፡
  4. የጨረታ ቦታዎችን በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በተለጠፈው ኘላን መመልከትና በአካል መጎብኘት ይቻላል፡፡
  5. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የደብረ ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here