ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
81

ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ ለ2017 ዓ.ም የተጠቃለሉ ህጎች ቅጽ 4 ህትመት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የተጠቃለሉ ህጎች ቅጽ 4 ህትመት በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው ነገር ግን ከላይ ከ1-2 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል አብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 /ከገንዘብ ያዥ ቢሮ/ መግዛት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን ዋጋ የተጠቃለሉ ህጎች ቅጽ 4 ህትመት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ማህተማቸውንና ፊርማችን በማሰፈርና ፖስታውን በሚገባ በማሸግ ለአብክመ ፍትህ ቢሮ ግዥ ባለሙያዎች ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ 15/07/2017 እስከ 30/07/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ  3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አብክመ ፍትህ ቢሮ ቁጥር 04፣ በ16ተኛው ቀን በ30/07/2017 ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. በሚገዙ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግት ፍትህ ቢሮ

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here