ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

በደ/ጎንደር ዞን የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግን/አስ ቡድን በ2017 በመደበኛ በጀት ለሰዴ/ሙ/ወ/ው/ኢ/ጽ/ቤት ለአዳዳ ከተማ ህዝብ አገልግሎት የሚውል የውሃ ፓምፕ እና ሞተር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ፡-

  1. በየዘርፉ ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200‚000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በሥራ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ አስር በመቶ የውል ማስከበርያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀን በጋዜጣ ተለጥፎ ይውላል፡፡
  11. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ይታሸጋል፣ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ጨረታውን ለመክፈት ቢገኙም ባይገኙም ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  12. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
  13. ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  14. በማስታወቂያ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  17. የጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደርያ ሃሳብ ላይ ለወጥ (ማሻሻያ) ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 28 07 69 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here