በአብክመ በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በUNDP በጀት በስሩ ለሚገኙ ለጃ/ወ/ውሃ እና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የውሃ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርትፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1–3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃወቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 0.5 በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ከ15/07/2017 ዓ/ም እስከ 29/07/2017 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከ15/07/2017 እስከ 29/07/2017 ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 30/07/2017 ዓ/ም 9፡00 ታሽጎ 9፡15 ይከፈታል፡፡ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታው ይከፈታል ፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ሲሆን ለ30 ተከታታይ ቀናት ፅንቶ ይቆያል ፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ-ብርሃን ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው የሚያስረክቡ ሲሆን ትራንስፖርት ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፤ እንዲሆም የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 0582940023/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት