ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
91

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ የእንስሳት መደሃኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሎት 1 የእንስሳት መድሀኒት ግዥ እና ሎት 2 ቴትራ የእንስሳት መደሀኒት 3400 ሚ.ግ ፣3200 ቦክስ ሽያጭ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የግዥው መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይጠበቅቦታል፡፡
  4. ከላይ ከ1-3 የተዘረዘሩትን የምታሟሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 8 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዩኒየኑ ዋና መሥሪያ ቤት /ሂሳብ ክፍል/ እስከ 8፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  6. የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ የእንስሳት መድኃኒት ግዥ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል የዋጋ ድምር ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
  12. የማስረከብያ ቦታ ዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ ቡሬ ከሚገኘው ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኔዬን ኃ.የተ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here