ግልጽ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
99

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8/1 መሰረት በ2017 በጀት አመት በ2ኛ ዙር ጨረታ በመኖሪያ ብዛት 24 ፣ በማኒፋክቸሪግ ብዛት 2 ፣ አጠቃላይ 26 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10 ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተወካዮችም ሆኑ ግለሰቦቹ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በነፋስ መውጫ ቀበሌ 03 ኢ/ል/ከ/አገ/ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  5. ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
  6. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በጽ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 01 92 ወይም 058 445 13 60 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቦች /ህጎችን/ ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. መ/ቤት ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here