ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
183

በአብክመ ግብርና ቢሮ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ለ2017 የበጀት ዓመት ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች ለምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል የማገዶ የእንጨት ጭነት አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የማገዶ  እንጨቱ የሚገኝበት ቦታ ከደሴ ዙሪያ ወረዳ ዳባመግለቢያ ከዋናው መንገድ ወደ ጎን በመግባት 5 ኪሎ ሜትር ወደላይ ገባ ብሎ ሲሆን የማገዶ እንጨቱም የሚጓጓዘው ኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ድረስ ሲሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. ከላይ የተገለጸውን አቅርቦቶች እና የጭነት አገልግሎት ለማቅረብና ለመስጠት አግባብ የሆነና በየዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና ከ200,000/ሁለት መቶ ሽህ/ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ በደንብ በሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር በተናጥል A4 ወረቀት በማያያዘ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፀውንና በዘርፉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በብር 200/ሁለት መቶ/በመክፈል ክኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 10 መግዛት ይቻላል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የጨረታውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡ ከዚህ ውጭ ያቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይደረጋል፡፡
  4. ተጫራቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከ15/07/2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ 29/07/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 12 ዘወትር በስራ ሰዓት በጥሩ ሁኔታ በታሸገ ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል በማለት የድርጅታቸውን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም በዚህ ቀን ከቀኑ በ8፡30 በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ አሸናፊነቱ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ካስያዘ በኋላ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑ ይታወቅ ፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0335510186 /0335514206/07 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኮምቦልቻ ግብርና ከሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here