ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
109

የመተማ ደም ባንክ አገልግሎት በ2017 በጀት አመት ለተቋሙ የሚያስፈልጉ ሎት1. እስቴሽነሪ፣ ሎት2. የፅዳት እቃ፣ ሎት3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ሎት4. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ፣ሎት5. የፈርኒቸር አቃዎች ግዥ ለመፈጸም በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡

  1. ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ያላቸው።
  3. የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ/ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ንግድ ፈቃዳቸውን ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ከዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ጋር ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  6. ከጠቅላላ ዋጋው 1በመቶ በባንክ ከተረጋገጠ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤቱ  በመሂ 1 በመክፈል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ከ15/07/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 29/07/2017ዓ.ም ድረስ በመተማ ደም ባንክ ቢሮ ቁጥር 03 የማይመለስ ብር 20

(ሃያ) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ በመግዛት ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ እስከ 30/07/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፤00 ድረስ በግዥ/ፋ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 03 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
  2. የጨረታ ሳጥኑን በ30/07/2017 ዓ.ም በ4፡00 በመተማ ደም ባንክ በግዥ/ፋ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 03 የጨረታዉ ሳጥን ታሽጎ በ4፡15 ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል ።
  3. ተጫራቾች ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ መፈረም እና ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ማንኛውም ተጫራች የመስሪያ ቤቱን ሰነድ በሌላ ሰነድ መቀየር እና በዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸውም ፤ በአጋጣሚ ስርዝ ድልዝ ካለው ስለ ትክክለኛነቱ ፊርማ መኖር አለበት
  5. በኮፒነት የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ የኦርጅናል ፎቶ ኮፒ መሆን ይኖርበታል።
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡
  7. አሸናፊው የሚለየው በሎት ( በጥቅል ) ይሆናል ፡፡
  8. አሸናፊው ግለሰብ እቃዎችን ገንዳ ውሃ ድረስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  9. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0583270486 ወይም 0918402788 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የመተማ ደም ባንክ አገልግሎት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here