የምዕከላዊ ጎንደር አስተዳደር ዞን የምዕራብ በለሳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓ/ም ለምዕራብ በለሳ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በሴፍትኔት የኑሮ ማሻሻያ በጀት ድጋፍ ለፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች የመስኖ ልማት የውሃ ማሰባሰብ አገልግሎት የሚውል 100 (አንድ መቶ) የውሃ መሳቢያ ሞተር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ይህን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች /አቅራቢ ድርጅቶች/ እንድትወዳደሩ እየጋበዝን፡- በዚህ መሠረት ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን 15/07/2017 ዓ/ም እስከ 14/08/2017 ዓ/ም 11፡30 ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ለተከታታይ 30 ቀናት
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ስርዝ ድልዝ ሣይኖረው በመሙላት በሁለት ፖስታ ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጉልህ በፖስታው ላይ በመፃፍ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ክብ ምህተም ፣አድራሻ ፣ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ምዕ/በ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሣጥን በ15/08/2017 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ በ4፡30 ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከፊት ለፊቱ ልዩ ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ ምዕ/በ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለእለት ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሠኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሠነድ ጋር አያይዞ ከጨረታ ሣጥኑ ከኦርጅናል ሠነድ ጋር ማስገባት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ የጨረታው ውጤት ከታወቀ የመደን ድርጅት የሚቀርብ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በባንክ ቸክና ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ ከፈለጉ ምዕ/በ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 09 70 11 12 04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው በክልሉ ገ/ኢ/ል/ቢሮ ባወጣው የግዥ መመሪያ የሚተዳዳር ይሆናል፡፡
- ሁሉም እቃዎች በጥራት ኮሚቴ ትክክለኛነታቸውን ሲረጋገጥ ገቢ ይደረጋሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ምዕ/በ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ከረዳት ገንዘብ ያዥ 100 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
የምዕራብ በለሳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት