የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ከCIP- የካፒታል በጀት የመንገድ ዳር መብራት ጥገና እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ ተለይቶ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 13 በ16ኛዉ ቀን 3፡00 ታሽጐ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዛወራል፡፡
- የመንገድ ዳር መብራት ጥገና እቃ ግዥ አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ግዥው የሚፈጸመው መሥሪያ ቤቱ /ግዥ/ ፈጻሚው በሚያቀርበው ናሙና ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 61 24 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ማንኛዉም ህጋዊ ተጫራች የማይመለስ 1000 /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የመንገድ ዳር መብራት ጥገና እቃ ግዥ ወጭዎችን የሚሸፍነዉ አሸናፊ ተጫራች ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን
ባሕር ዳር