ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
80

ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን በበጀት አመቱ ከሚያሰራቸው ፕሮጀክቶች መካከል በ6 (ስድስት) ቦታዎች ላይ የትራፊክ መብራት ጥገና ሥራ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች በኤሌክትሮ መካኒካል ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 2 መሆን አለባቸዉ፡፡
1. የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
2. ከላይ የተጠቀሰውን ፕሮጀክት ለማሰራት አስፈላጊውን ሁሉ የሰው ሃይል የማቴሪያል እንዲሁም የመሳሪያ አቅርቦቶችን የሚያሳይ በስማቸው የታሸገ የፋይናንሽያል እና የቴክኒካል የመወዳደሪያ ሃሳቦችን ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 የማይመለስ ብር 2000 /ሁለት ሽህ ብር/ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች የተጫራቹንና የኘሮጀክቱን ስም በግልጽ ተቀባይነት ባለው የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ የተጫራቾች መመሪያ ተ.መ 21.1 ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
5. ተጫራቾች መመሪያ በማንበብ ሙሉ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ይመከራሉ፡፡
6. ኘሮጀክቶች የሚጠናቀቁበት ቀን በክፍል 8 አንቀጽ አ.ዉ.ሁ 72.1 ላይ በተገለፀዉ ቀን መሰረት ይሆናል፡፡
7. ሁሉም የቅድመ ማጣሪያ /ቴክኒካል/ እና ጨረታ ዋጋ /ፋይናንሻል/ ሰነዶች በተለያዩ ኢንቨሎፓች ማህተም በማድረግ መታሸግ ይኖራባቸዋል (አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ)፡፡
8. ጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል፡፡ የመጀመሪያው ሂደት /ደረጃ የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴክኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በቁጥር አብክመ ዝ/ቢ/ኮቢ-01/02 በቀን 15/09/2014 ዓም በተሻሻለዉ መመሪያ መሰረት ዝቅተኛ የጨረታ ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ ይህን መመሪያ በደንብ ያንብቡት፡፡
9. የታሸጉ የቅድመ ማጣሪያና የጨረታ ዋጋ ሰነዶች የሚቀርቡት ለመንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ሆኖ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ2፡30 ጀምሮ እስከ 22ኛ ቀን ሳጥኑ እስኪታሸግ ድረስ ሲሆን ጨረታው በይፋ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን 3፡00 ታሽጐ 4፡00 ላይ በግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
10. ተጫራቾች ማንኛውንም ተጨማሪ መረጃ ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ስልክ ቁጥር 0533201878/0583203246 ማግኘት ይችላሉ፡፡
11. በባህር ዳር ከተማ ውስጥ በባለፈው አመት ውስጥ ፕሮጀክት ጀምሮ ያቋረጠ ወይም በተሰጠው ውል መሰረት ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ያሉት ተጫራች በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችልም፡፡
12. ማንኛውም ተጫራች ከሥራ ዝርዝሩ ውስጥ ወይም ከዚህ በላይ የሥራ አይነቶች ላይ የነጠላ ዋጋ ሳይሞላ ቢቀር ያለ ክፍያ ሥራውን እንዲሰራው ይገደዳል፡፡
13. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከማስገባቱ በፊት የሳይት ጉብኝት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ አሰሪ መሥሪያ ቤቱ ከሳይቱ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን አይቀበልም፡፡
14. ማንኛዉም ተጫራች በሚሞላዉ ሰነድ ላይ የሚፈጠር ሥርዝ ድልዝ ከዉድድር ዉጭ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መደበኛ የጨረታ ሰነድ ለግንባታ ሥራዎች ግዥ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተዘጋጀ 2011 ዓ.ም መረጃ ከሰነዱ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይመልከቱ፡፡
15. ተጫራቹ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ አገልግሎቶች ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ በቁጥር ቢያንስ 3 (ሶስት) ማቅረብ አለበት፡፡
16. የባ/ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
17. ከጨረታው አሸናፊ ሰባት ነጥብ አምስት ቫት ተቀንሶ የምናስቀር መሆኑን እንዲታወቅ፡፡
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን
ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here