ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
75

የአዴት ሆስፒታል የግ/ዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የምግብ አቅርቦት፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም ሎት 4 የሰራተኞች ሰርቨስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንጋብዛለን፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው፡፡
4. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የሚገዙት የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሰፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት ይቻላል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአዴት ሆስፒታል በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 22/07/2017 ዓ.ም እስከ 06/08/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው በቀን 07/08/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል፡፡
11. መ/ቤቱ ከጨረታው ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ (ሎት) የሞላው ነው፡፡
13. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ለበለጠ መረጃ ቢሮ ቁጥር 08 በአካል ቀርበው ማነጋገር ይቻላሉ፡፡
የአዴት ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here