የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
75

የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት በ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ 5 ለድርጅት 1 የድርጅት ልዩ ጨረታ 1 በድምሩ 7 ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል በመሆኑም፡-

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል አ/ዘ/ከ/አስ/መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ማስታወቂያው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሸት 11፡00 ብቻ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ከጠዋቱ በ3፡00 ይሆናል፡፡
  5. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 31 73 72 ወይም 09 27 60 08 17 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  6. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here