ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
81

አብክመ ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣የኮምፕረሰር እቃ እና ጋዝ መሙላት ግዥ ፣የመፀዳጃ ቤት እድሳት ግዥ እና የአትክልት ማስቀመጫ ከተመረጡ ዛፎች ጋር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) አና በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ፣ የኮምፕረሰር እቃ እና ጋዝ መሙላት ብር 35,000 /ሰላሳ አምስት ሽህ ብር/ ፣የመፀዳጃ ቤት እድሳት ብር 3,500.00 /ሶስት ሽህ አምስት መቶ ብር/ እና የአትክልት ማስቀመጫ ከተመረጡ ዛፎች ጋር 6,500.00 /ስድስት ሽህ አምስት መቶ ብር/ የሚወዳደሩ ከሆነ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት በአብክመ ገቢዎች ቢሮ ቁጥር 313 ኤሌክትሮኒክስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር)፣ የኮምፕረሰር እቃ እና ጋዝ መሙላት፣ የመፀዳጃ ቤት እድሳት እና የአትክልት ማስቀመጫ ከተመረጡ ዛፎች ጋር የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር ) ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6:30 ጨምሮ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
7. አስራ ስድስተኛው (16ኛዉ) ቀን ቅዳሜ ፣እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
8. የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል፡፡
9. ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
አድራሻችን፡- ባህር ዳር ቀበሌ 16 ሜድሮክ ጀርባ እና የድሮው ዶ/ር ፍሬው የነበረው የአሁኑ ዶ/ር አዲሱ ክሊኒክ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 058 226 57 65 ወይም 058 226 61 71 መጠቀም ይቻላል፡፡
አብክመ ገቢዎች ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here