ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
74

ድርጅታችን መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተ ጤፍ የአንዳቤት እና የእስቴ ምርት የሆነ 600 (ስድስት መቶ) ኩ/ል ነጭ ጤፍ እና 600 (ስድስት መቶ) ኩ/ል ሰርገኛ ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየጋበዝን፡-

  1. በዚህ ንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ከመንግስት የሚጠበቀረባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ መገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን እና ተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በመክፈል በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ ፣ስማቸውን ፣ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-4 የተዘረዘሩትን ሰነዱን በመግዛት ዋጋቸውን ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተሸጦ በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 10ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. የማስረከቢያ ቦታ ዩኒዬኑ መጋዘን ደብረ ታቦር ላይ ማቅረብ የሚችል ሲሆን የጨረታ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ ናሙናውን ማየት እና በናሙናው መሰረት መሆኑን ከመጫኑ በፊት ከቦታው የዩኒዬኑ ባለሙያ ሲያረጋግጥ ብቻ የሚጫን ሲሆን በ10 ቀን ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ የሞላው ሲሆን አሸናፊው በተለየ በ5 ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪ የዋጋውን አስር በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡
  8. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 28 64 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here