በአብክመ በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1 5,000 ኩ/ል የዳቦ ስንዴ ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ፣ሎት 3 የደንብ ልብስ ግዥ ፣ሎት 4 የፋብሪካ መለዋወጫ ዕቃ ግዥ ፣ሎት 5፡ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርት መለኪያዎች /ሚዛን/ ግዥ ፣ሎት 6 ለቢሮ ፣ለባንክ ወይም የሱቅ ማከራየት ግዥ ፣ሎት 7 የምግብ ፋብሪካ የጥራት መለኪያ መሳሪያዎች ግዥ እና ሎት 8 የዱቄት ፋብሪካ ሻዉርና ሽንት ቤት ጥገና ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ በማዉጣትና በማወዳደር ከአሸናፊ ድርጅቶች መግዛት ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
3. ጨረታው ግልጽ ጨረታ በብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አይደለም፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም የሚያይዟቸዉ ሰነዶች በአግባቡ የሚነበቡ መሆን አለበት፡፡
5. ሎት 8 ላይ የሚወዳደር ተወዳደሪ የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ ሰባ እና ከዚያ በላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
7. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 /ሶስት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣዉ ለዳቦ ስንዴ ግዥ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላሉ፡፡ እንዲሁም ለሁለተኛ ጊዜ ለወጡት ከሎት 2 እስከ ሎት 8 ለተጠቀሱት ደግሞ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሂሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላሉ፡፡
8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሎት 1 ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣዉ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፡፡ በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ለወጣዉ ደግሞ ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
9. ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
10. ጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
11. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
12. ከአንድ ሎት ውስጥ የንግድ ፈቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም ፣አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመር (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡
13. አሽናፊው የአሽነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ሊያስረክብ ነው፡፡ ለስራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊ ይሸፍናል፡፡
14. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
15. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
16. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 11 59 05 34 / 09 18 27 83 96 መጠየቅ ይቻላል፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.