የአዲስ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ከግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የጥበቃ ሥራዉን አዉትሶርስ አድርጎ ለአንድ አመት ሥራውን እያሰራን የቆየንና ለ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በአዲስ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ዉል በመዉሰድ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጨረታ የሚወዳደሩ ድርጅቶች ማለትም፡-
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና ለጥበቃ ሥራ ከፌደራል ፖሊስ የሚሰጠው የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- አጠቃላይ የአንድ አመቱ ድምር የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አጠቃላይ ስለ ጥበቃ ሥራው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሆስፒታሉ ዋና ገ/ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት በመግዛት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የጥበቃ ሥራ ጠቅላላ የአንድ አመት ዋጋ ግምት ማንኛውንም ግብር እና ታክስ ጨምሮ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ኮፒውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱን ወር ዋጋና የ12 ወራት ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ሆኖ በ16 ቀን እስከ 3:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 3፡00 ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኝም በሆስፒታሉ አዳራሽ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል /ዝግ/ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ሲሆን መረጃው ከተገኘ እጩ ተጫራቾች ከጨረታ ውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 03 71 /09 18 02 46 84 /09 18 61 70 63 /09 49 65 55 86 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአዲስ ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታለል