የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በዋድላ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሥር ለሚገኘው 1ኛ የቋና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አገልግሎት የሚውል የመማሪያ ክፍል የፊኒሽንግ ሥራ /ግንባታ/ በመደበኛ በጀት፣ 2ኛ በዋን ዋሽ ፕሮጀክት በጀት የታድላ መንደር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቆርቆሮ በቆርቆሮ የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ እና 3ኛ የታድላ መንደር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የውሃ መስመር ዝርጋታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች /ድርጅቶች/ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ መረጃ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እና ለግንባታው ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተዘጋጀው ጨረታ የሥራ ዝርዝር ሰነድ መሰረት መስራት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የተዘጋጀውን እያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ይህ ግልጽ ጨረታ ከቀኑ 8፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ለግንባታው በ22ተኛው ቀን በተጠቀሰው ስዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የወሰዱትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ ለእያንዳንዳቸው ማለትም ለሶስቱም ሥራዎች ለየራሳቸው /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤቱ በመሂ 1 ገቢ የተደረገ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታውን በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
- ስለጨረታው ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 20 01 39 41 /09 35 21 60 96 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት