የግዥ መለያ ቁጥር መ/ግ/04/2ዐ14
በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን እና ለሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ለ2017 በጀት አመት የሚውሉ የአላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን ጥቅል ግዥ ማለትም ሎት1.የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት2.የፕሪንተር ፣የፎቶ ኮፒ ቀለሞች /ቶነሮች/ ፣ሎት 3. የመኪና ዲኮር /ጌጣጌጥ/ እና የታፒሴሪ ዕቃዎች ፣ሎት4. የጽዳት እና መዋቢያ ዕቃዎች ፣ሎት5. የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ፣ሎት 6.የሕንፃ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ሎት 7.የፈርኒቸር/የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) በከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00 /አንድ መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት በፓስታ በማሸግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት እና በ16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582209644/0582209646 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን