የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2017 በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርቴፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የወጣው ጨረታ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ግዥ ከብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ ሁለት በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ተገቢውን የውል ማስከበሪያ ከባንኮች በተረጋገጠ የጠቅላላ ግዥ ዋጋ አስር በመቶ ሲፒኦ በማቅረብ ውል መያዝ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በአንድ በታሸገ ፖስታ በደ/ማርቆስ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛ ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሲሆን ተጫራቾች በተገኙበት /በተወካይ ፊት ይሆናል፡፡
- ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡- ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ ቁጥር 09 20 50 43 80 /09 20 5068 87 /09 37 37 28 10 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት