በአፈ/ከሳሽ አስሬ ቸኮል እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አልማው ታፈረ መካከል ስላለው የገንዘብ ከርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 04 በሰሜን ባንቲገኝ ቢተው ፣በደቡብ መንገድ ፣በምስራቅ ሙሉነህ ባንቴ እና በምእራብ አትንኩት ባንቴ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው እና በአፈ/ተከሳሽ በአቶ ግርማው ሞገስ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው መኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 501,250/አምስት መቶ አንድ ሽህ ሁለት መቶ ሀምሳ/ ብር በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ከመጋቢት 29/2017 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም ድረስ ቆይቶ ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡00 እስከ 5፡30 ስለሚሸጥ ፤መግዛት የምትፈልጉ በቦታው በመገኘት መግዛት ትችላላችሁ፡፡ ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ውን በሲፒኦ አስይዛችሁ እንድትቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የአዊ ብሔ/አስ/ከ/ፍ/ቤት