የጎንደር ከተማ አሰተዳደር ጤና መምሪያ ስር የጠዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በሎት1. የፋርማሲ ማስፋፊያ ግንባታ የእጅ ዋጋ እና ማቴሪያልን ጨምሮ በማቅረብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ምዝገባ ሰርትፊኬት ያላቸው፡፡
- ሁሉም ተጫራች የመልካም ስራ አፈፃፀም መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ሁሉም ተጫራች የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በከተማ ልማት የግንባታ ምስክር ወረቀት ከደረጃ 7 እና በላይ የሆናችሁ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጠዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡ/መሪ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ስዓት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ/ወይም በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ በጠዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጠዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡ/መሪ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ከ29/07/17ዓ እስከ 19/08/17ዓ.ም ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 10፡30 ታሽጎ በ22ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይከፈታል፡፡
- የስራ ዝርዝር /ስፐስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው፡፡
- በጨረታው ላይ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 0584480333 ደውለው መጠየቅ ወይም ጠዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡ/መሪ ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ጠዳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ