ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
89

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ Lott 1 butt fusion welding machine from 63mm up to 250mm and 160mm up to 400mm እና ሎት 2 የተሸከርካሪ መኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ /የታደሰ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናል፣ ኮፒውን፣ ፋይናሻል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር ለየብቻ በማሸግና ሁሉንም በአንድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /un Conditional Bank Garanty ከቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም እቃውን ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር  05 83 20 50 79  ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  11. አድራሻ ቀበሌ 08 ዋናው የባሕር ዳር ከተማ የመ/ወው/ፍ/አገ/ድርጅት

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here