ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
94

የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለምዕ/ጎጃም ዞን መምሪያዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን በስድስት ሎት በማደራጀት ማለትም ሎት 1 ጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ ቀለም፣ ሎት 3 ፈርኒቸር፣ ሎት 4 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 6 የቀላል መኪኖች ጎማ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ህጋዊ አቅራቢዎችን በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ ዝርዝር ስፔስፊኬሽን እና ሳፕል መሠረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ከሎት 5 ከኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በስተቀር በቀረበው ዝርዝር መሠረት በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ነው፡፡ አንድም ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡ ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አሸናፊ የሚለየው በተናጠይል ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ዝቅጠኛ ያቀረበው ሲሆን በጥቅል ድምር አሽናፊ ለሚለይባቸው ዕቃዎች ለአንድም ዕቃ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /አምሳ ብር/ የሚሽጥ ሲሆን ሰነዱ ከተቋማችን ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ/ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ት/መምሪያ በ3፡30 ታሽጉ በ4፡00  ይከፈታል እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆኑ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ በሲፒኦ አስር በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ መምሪያ ማስያዝና ዕቃዎችን ምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍሎች የማጓጓዣ ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ ሃያ በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
  14. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢ/ትብብር መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05 87 75 08 95 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይችላሉ፡፡

የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here