ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
113

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልል ም/ቤት ጽ/ቤት የአዳራሽ ጥገናና እድሳት (ሪኢኖቬሽን) ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፤ ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ የጨረታ ሰነድ በ500 ብር በመግዛት የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችህ፡፡

  1. All contractors of category GC-2/BC-1 and above, Special contracctor that have license in (interior design, Electromechanical, wall, floor, landscape and sanitary) single entity or joint venture contractor with license valid for the year 2017 E.C and can present registration certificate for construction work service from concerned organization.
  2. More than one joint venture is not allowed.
  3. ተጫራቾች በዘርፋ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ስም፣አድራሻ የሚመለከተው ወይም ህጋዊ ወኪል የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራጮች በጨረታ ሰነዱ የተቀመጡ ቴክኒካል መመዘኛዎችን ማሟላት አለባቸዉ ፤ቴክኒካል ሰነድ የማያሟሉ ተጫራቾች ፋይናንሽያል ሰነዱ ሳይከፈት ተመላሽ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራጮች ፋይናንሽያልና ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ዋናዉንና አንድ ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. በጨረታው የተሳተፈ ማንኛውም ድርጅት ዋጋ ካቀረበ በኋላ ዋጋውን መለወጥና ማሻሻል ወይም በጨረታው አልሳተፍም ቢል ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተመላሽ አይሆንም፡፡
  8. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡበት አጠቃላይ ዋጋ 2በመቶ በባንክ በተመሠከረለት የደረሰኝ ክፍያ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት አስገዳጅ የሆነ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞዴል 85 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ለማሸነፍ እንዲረዳው ከማንኛውም ኃላፊና ሰራተኛ ጋር አስፈላጊ ያልሆነ የጥቅም ግንኙነት ቢያደርግ ወይም ለማድረግ ቢሞክር ከጨረታው ይሰረዛል ፣በህግ ይጠየቃል፡፡
  12. ተወዳዳሪዎች ከተሸነፉ ያስያዙት ቢድ ቦንድ እንዲለቀቅ በጸሁፍ ሲያሣውቁ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ ስለ ትክክለኛ ስራ አፈጻጸም ዋስትና (Performance Bond) ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ በሚቀጥለው 10 ተከታታይ ቀን  በሲፒኦ  ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል ይፈጽማል፡፡ ዉል ካልፈጸመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራጮች ከአሁን በፊት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት እገዳ ያልተደረገባቸው መሆን አለባቸው፡፡
  15. ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶች የስራ እድል አማራጮችን ለማስፋትና ለማበረታት የተዘጋጀ መመሪያ ቁጥር 52/2014 ዓ/ም መሰረት የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን፤ ያላቀረቡ ተጫራጮች ከዉድድር ዉጭ ይሆናሉ፡፡
  16. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንዲሆን ተደርጐ የድርጅቱ ስም ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ይተላለፋል፡፡
  17. በጨረታው ለመሣተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  18. የጨረታ ማስከበሪያዉ ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ካለፈ በኃላ ለ20 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  19. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን አንስቶ እስከ 21ኛው ቀን ከጥዋቱ 2፡00 ድረስ የጨረታ ፖስታውን ለአማራ ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት በተዘጋጀዉ ሳጥን ገቢ ማድረግ አለባቸዉ፡፡ በዚሁ እለት 2፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  20. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  21. ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊው ተለይቶ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  22. የመጫረቻ ሰነዱ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ ለ20 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  23. Bidders must provide certificate of satisfactory execution of previous contracts and/or experience provided by other contracting parties to the contract concerned in number and within the period specified in the bid data sheet for similar size/type contract with a budget of at least that of this contract.
  24. Bidders must provide all relevant documents for equipments specified in data sheet.
  25. መ/ቤቱ የስራውን 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  26. ተጫራቾች ስለስራዉ አይነትና መጠን ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ጨረታ ከሚከፈትበት ቀን አስቀድመዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  27. የዋጋ መሙያዉ ስርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  28. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  29. ሌሎች በዚህ መመሪያ ያለተገለፁ በጨረታ ሰነዱ እና በመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ተገዥ ይሆናል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0582262151 /0582221438 ፖ.ሣ.ቁ 1324 መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የአብክመ የክልል ም/ቤት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here