በቆሻሻ ማጠራቀሚያ የሚጣል ከፍተኛ መጠን ያለውን ያገለገለ ጐማ በተለመደው ዳግም ለተመሳሳይ አገልግሎት የማዋል ሂደት ከሚያስከትለው ብክለት በፀዳ አዲስ ዘላቂ አማራጭ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚቻል ሳይንስ ዴይሊ ድረገጽ አስነብቧል::
በአሜሪካ የሰሜን ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ ለንባብ እንዳበቃው በአገሪቱ በ2021 እ.አ.አ ብቻ 274 ሚሊዬን ጐማ አገልግሎት ላይ ውሏል:: ከዚህ ውስጥ አንድ አመስተኛው በቆሻሻ ሲጣል ቀሪው ዳግም ለተመሳሳይ አገልግሎት እንዲውል ተደርጓል::
የካሮላይና ዩኒቨርሲቲ ተመራማራዎች ግን በቆሻሻ ጉድጓዶች የሚጣለውን ያገለገለ ጐማ በአዲስ ስልት በዘላቂ አማራጭ አገልግሎት ላይ የማዋል የምርምር ውጤትን ነው ይፋ ያደረጉት:: በዚህም
ዶክተር አሌክሳንደር ዚክሆቪትስኪ፣ ዌልያም አርኬናን እና ሌሎች ባልደረቦቻቸው ያገለገለ ጐማን ለማጣበቂያ ሙጫ (EPOXY RESINS) ማዋል የሚያስችል አዲስ ዘላቂ አማራጭን አስተዋውቀዋል::
እስከ አሁን ሲሰራበት የነበረው በዋናነት ያገለገለ ጐማን ለዳግም አገልግሎት በማብቃቱ ሂደት “በፖሊመር” ስሪት ውስብስብነት የተነሳ ጥቅም ላይ ማዋል አስቸጋሪ እንደነበረም ነው የተመላከተው::
በዚሁ የኘላስቲክ የጀርባ አጥንት የሆነውን ማጠንከሪያ ይዘቱን ለማላላት የመሞከር ሂደት ዝቅተኛ እሴት ያለው ውጤትን ማስገኘቱም ነው በአሉታዊነት እጥረት ሆኖ የሰፈረው::
በመጨረሻም ዋና ተመራማሪ እና የምርምር ቡድኑ መሪ ዶ/ር ዙክሆቪትስኪ አዲሱ የምርምር ስራቸው ከዚህ በፊት የተጠቀሱትን ፈተናዎች በአሸናፊነት ለመወጣት የሚያስችል ስልት መሆኑን ነው አፅንኦት ሰጥተው ያሰመሩበት::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የመጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም