በቀለሙ ከአጥቂዎች የሚሰወረው

0
77

ፀጉር አልባው አባጨጓሬ ተፈጥሮ በቸረችው ቀለማትን የመለየት ዓቅም ከዳራው ጋር በመመሳሰል ከአጥቂዎቹ መሰወር እንደሚችል ኦዲቲ ሴንትራል ድረገጽ ሰሞኑን አስነብቧል::

እስያ፣ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካን በመሳሰሉ ሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ባሉ ሀገራት በብዛት መገኘቱ የተረጋገጠው ሽምልምሉ የአባጨጓሬ ዝርያ ከዳራው ጋር በመመሳሰል ራሱን ከጥቃት መከላከል እንደሚችል የሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ ኘሮፌሰር ኢሊክ ሳፔሪ አረጋግጠዋል::

የአባጨጓሬ ዝርያዎቹ በአእዋፍ ከመበላት ለመዳን በቅጠሎች ወይም ቀንበጦች እና በቅርንጫፍ እንጨቶች ላይ ካሉበት ዳራ ጋር ቀለማቸውን ማመሳሰል ይችላሉ- ኘሮፌሰሩ እንዳብራሩት::

የነፍሳት ዝርያዎቹ አካላቸው እንደ ልምጭ ቀጠን ብሎ እንደሸንኮራ አገዳ በተወሰነ ልኬታ ልዩነት ክርክራት አለው:: ያ መሆኑ በተከፋፈለው አካላቸው  ልዩነት አስደናቂ ተፈጥሯዊ ቀለም መለያ ያላቸው መሆኑ ከሌላው ፍጥረታት ልዩ እንደሚያደርጋቸው ነው ያስታወቁት- ኘሮፌሰሩ::

ከዓመቱ በአJዛኛው በበጋ ወቅት ከእንቁላል እንደሚፈለፈል የጠቆሙት ተመራማሪው ንቁ ሆነው ከሀምሌ እስከ መስከረም ወር ሲንቀሳቀሱ በቅጠልም ሆነ በቅርንጫፎች ላይ ስለማይለዩ በቀላሉ ማየት እንደማይቻል ነው እማኝነታቸውን የሰጡት::

ዝርያዎቹ ከአጥቂዎች ጭንቅላታቸውን እና በመጨረሻ አካላቸው ላይ ባለው አጫጭር እግር ቅጠል ወይም ቅርንጫፎች ላይ ተጣብቀው ከቀንበጥ ወይም ቅርንጫፍ ጋር ተመሳስለው በማሳሳት ከጥቃት ይድናሉ::

በአንድ ቅርንጫፍ ወይም ቅጠል ላይ ቀለማቸውን አመሳስለው በያዙት ቅርፅ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየትም ይችላሉ:: ይህም አባጨጓሬዎቹ ህይወት ዓልባ ናቸው ብለው እንዳያጠቋቸው ራሳቸውን የሚያድኑበት ተፈጥራዊ ስልት መሆኑን ነው ተመራማሪው ያሰመሩበት::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here