የእብናት ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለእብናት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ በህብረት 1ኛ ደረጃ G+1 ባለ 10 የመማሪያ ክፍል ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ ድምር 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ በእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ጋራንት /በጥሬ ገንዘብ/ እብናት ወረዳ ገ/ኢ/ል /ጽ/ ቤት ዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ ኦርጅናል ሰነድ እብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥና ን/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 06 ባዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታዉ ማስታወቂያውበጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ ለ21 ቀናት ቆይቶ በ22ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና/ን/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 06 ጨረታው በወጣ በ22ኛው ቀን ከሰአት 8፡30 ታሽጎ 9:00 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ
/የህዝብ በአል ከሆነ/ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡ - አሸናፊው ለስራ በተፈለገበት ስዓት ለ3 ቀናት ተጠብቆ ካልቀረበ በመመሪያ መሰረት መ/ቤቱ እርምጃ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር በሚሞሉበት ስዓት ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከጨረታ
ውጭ ያደርጋል፡፡ - የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 08 የማይመለስ 500 ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- አሸናፊው እንደተለየ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ30 ቀናት ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0584400606 /218 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእብናት ወረዳ ገንንዘብና ኢኮኖሚ ትበብር