ሰማኸኝ ከበደ /የንግድ ስም ሰማኸኝ ከበደ መኩሪያ/ በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ በ031 ቀበሌ ልዩ ቦታው ሚጣይ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የግራናይት ማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
Adindan UTM Zone 37N
Geographic Coordinates of the license area
Point Id | X Coordinates | Y Coordinates | Area |
1 | 511345 | 1200549 |
170‚287m2 |
2 | 511029 | 1200893 | |
3 | 511066 | 1201093 | |
4 | 511574 | 1201051 |
አዋሳኞቹ
በሰሜን | በደቡብ | በምዕራብ | በምሥራቅ |
ደን | ከውዱ ቤት ስር ያለ ገደል | ወንዝ/ድልድይ | የአርሶ አደሮ መሬት |
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርብ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ