የግዥ መለያ ቁጥር 22/2017
ሱታና ንግድና የማማክር ስራዎች ኢትርፕራይዝ ለተማሪዎች የምግብ አግልግሎት የሚውል ጥራቱን የጠበቀ ቀጭ ቀጭ የሌለው ነጭ ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከሱታና ንግድና የማማክር ስራዎች ኢተርፕረይዝ ስራ ክፍል በመዉሰድ ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ /ፖስታ/ የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለይቶ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ኢንተርፕራይዙ ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 203 የምትጫረቱትን የአንዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ የሚገዛዉ ዕቃ ከ200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ሲሆን ፡፡ የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈውን ጤፍ የወዛደር ማውረጃ ጭምር ራሱ ችሎ ዩኒቨርስቲዉ ግቢ ድረስ በራሳቸዉ ወጭ በማቅረብና ማስረከብ አለባቸዉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000/አንድ መቶ ሽህ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፋቸዉ ውል መያዝ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ16 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያዉ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ፡፡
- በጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ ፡፡ አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7/ሰባት/ቀን በኋላ ባሉት 8 ቀናት ዉስጥ ዉል መያዝ አለባቸዉ ፡
- ኢተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ኢተርፕራይዙ 20በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- በለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 -11 -59 -13 -56 ወይም 09 -13- 42 -26 -44 ይደዉሉ፡፡ አድራሻ በአዊ አስ/ዞን እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ ነዉ፡፡
ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ