ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
81

የጨረታ ቁጥር አብክመ /ወኩምኤ/ብ/ግ/ጨ//04/2017

በአብክመ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ለአገልግሎት የሚውሉ ታብሌት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ  ህጋዊ  ንግድ  ፈቃድ  ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት )ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብየሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00 /መቶ /ብር በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሪት ዳይሪክተር ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች /ሎቶች/ 1 በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ከተጠቀሱት ዕቃዎች ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ከአንድ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል ኦርጅናል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥና ንብ /አስተ/ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይም ቢሮ ቁጥር 406 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ንብ /አስ/ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 406 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. የአገልግሎት መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 406 ድረስ

በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 31 58 ፋክስ 058  320  11 83  ፖ.ሳ.ቁ  965 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here