ባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማዕከል በስሩ ያሉትን የካፌና ሬስቶራንት ክፍሎች በዘርፉ ልምድ ያላቸዉን ድርጅቶች በመለየት በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ለጨረታ የቀረቡ ክፍሎች ብዛትና አገልግሎት በጨረታ ሰነዱ (ስፔፊኬሽን) የሚገኝ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000(አስር
ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ ተጨማሪ
ክፍል ለመከራየት ፍላጎት ያለው ተጫራች ለተጨማሪ ክፍሉ ሌላ ማስያዣ ማስያዝ አለበት፡፡ - የጨረታ ሰነዱ ባህርዳር ከተማ ሆምላንድ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የአብክመ
ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ግዥ፣ፋይ /ንብ /አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 11 ላይ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡ - የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በአሀዝና በፊደል መገለፅ አለበት፡፡ ሆኖም በፊደልና በአሀዝ የተሞላው ልዩነት ካለው በፊደል የቀረበው መወዳደሪያ ዋጋ ብቻ ለወድድር ይቀርባል፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሽያል መወዳደሪያ የዋጋ ማቅረቢያና የዋስትና ማረጋገጫ ሲፒኦ በፓስታ በማሽግ በአብክመ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት፣ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀና የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 222 22 70/058 226 21 77 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ማእከል