ለ81 ዓመታት የተመላለሰው ካርድ

0
90

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በ1940ዎቹ መጀመሪያ በተካሄደበት ወቅት የተገናኙ ጓደኛሞች ላለፉት 81 ዓመታት “የእንኳን ተወለድሽልን” መልካም ምኞታቸውን በአንድ ተመሳሳይ ካርድ በመላላክ መለዋወጣቸውን ዩፒአይ ድረ ገጽ ከሳምንት በፊት አስነብቧል::

የ“እንኳን ተወለድሽልን!” የልደት ካርድ ልውውጡ በአሜሪካ ኢንዲያኖፖሊስ ሜሪዊተን ለጓደኛዋ ፓት ዴሬመር ለ14ኛ ዓመት የልደት ቀኗ በሰጠችበት እለት ነው የተጀመረው::

የዛሬ 81 ዓመት በግንቦት ወር ደግሞ ፓት ዴሪመር በዚያው የመልካም ልደት መግለጫ ካርድ ላይ ፊርማዋን አኑራ መልሳ ለሜሪዊተን ትልከዋለች:: በዚህ መልኩ የተጀመረው የመልካም ምኞት መግለጫ ካርድ ልውውጥ 81 ዓመታትን አስቆጥሯል::

ሁለቱ ጓደኛሞች “እንዲህ እናድርግ” ብለው አስበውበት አለመጀመራቸውን ቃለ መጠይቅ ላደረገላቸው የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል:: ነገር ግን በየዓመቱ የልደት መታሰቢያ ቀናቸው ወይም እለት በተቃረበ ቁጥር ተደዋውለው ለማውጋት የማይዘነጋ መነሻ ምክንያት እንደሆናቸውም ነው በአፅንኦት የተናገሩት::

ሁለቱ ጓደኞሞች የመልካም ልደት መታሰቢያ ካርድ ልውውጥ የጀመሩበትን 60ኛ ዓመት ባከበሩበት ጊዜ ለዓለም ዓቀፉ የድንቃ ድንቅ መዝጋቢ ድርጅት አቅርበው ለረዢም ጊዜ “የእንኳን አደረሰሽ!” ካርድ በመለዋወጥ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here