ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግለጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
108

የግዥ መለያ ቁጥር ፡ አብክመ/ኢቴቢ/ግ/ጨ/06/2017

በአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለተለያዬ  አገልግሎት የሚውሉ ሶፍትዌሮችን ማለትም ፡-

  • ሎት1. የመንግስት ሰራተኞች የመረጃ አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር ልማት (ICSIMS)
  • ሎት2. ኢንቨስትመት አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር ልማት (IMS)
  • ሎት3. የቱሪዝም አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር ልማት (ITMS) በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስለማት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  3. የሚወዳደሩበት ሎት ግዥ ጥቅል ዋጋ ብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ስፔስፊኬሽን ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚለሙ ሶፍትዌሮችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በተቋሙ ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣትና የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን የሲስተም ልማት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን ፣የንግድ ፈቃድ ሰነድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና ተያያዥ ሰነዶችን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የፋይናንሻል (የዋጋ) ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሌላ ፖስታ በማድረግ ለየብቻ በታሸጉ 2 ፖስታዎች (ቴክኒካልና ፋይናንሻል በማለት) ማስገባት አለባቸው፡፡ ይህም የሚሆነው ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት 13/08/2017 ዓ.ም እስከ 27/08/2017 ዓ.ም) ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በ 27/08/2017 ዓ.ም ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በአል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው በሎት (ምድብ) ዋጋ  ይሆናል ፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች በቴክኒካል ሰነዳቸውና በፋይናንሻል ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ይህ ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ ፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583206856 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here