በሬሳ ማይኒንግ ኃ/የተ/ የግ/ ማህበር በሰ/ሸዋ ዞን አንሳሮ ወረዳ በሳላይሽ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎድጓዲት ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሲልክ ሳንድ ማእድን ምርመራ ሥራ ፈቃድ እንዲሰጣቸው መሥሪያ ቤታችንን ጠይቀዋል፡፡
የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶችም፡-
Adindan UTM Zone 37N
Geographic Coordinates of the license area
| Points | Easting | Northing |
| 1 | 491579 | 1087296 |
| 2 | 491466 | 1087372 |
| 3 | 491779 | 10875515 |
| 4 | 491838 | 1087388 |
| ብሎክ ቁ. | በሰሜን | በደቡብ | በምእራብ | በምስራቅ |
| 1 | የወል መሬት | የወል መሬት | የወል መሬት | የወል መሬት |
ስለዚህ የተጠየቀውን ፈቃድ ከመስጠታችን በፊት በተጠቀሰው አካባቢ በተለይም ከዚህ በላይ በተመለከቱት የጂኦግራፊክ ኮኦርዲኔቶች በሚከለል ቦታ ላይ ያገባኛል የሚል ካለ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት /07/ ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን በጽሑፍ ለመሥሪያ ቤታችን እንዲያቀርብ እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 222 12 37/21 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ

