የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግዥናን/አስ/ቡድን ለቢቡኝ ወረዳ እንስሳት ዓሳ ሀብት ፅ/ቤት የእንስሳት መድሐኒት በ2ዐ17 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመጫረት የሚፈልግ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡
- በአዲሱ አዋጅ መሠረት የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺ ብር/እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶኮፒ ለየብቻዉ በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የግዥ ፈፃሚው እና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨራታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የጨረታ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/በጥሬ ገንዘብ/ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የመድሀኒቱን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 200/ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨራታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የመድሀኒት አቅርቦት ብር ጠቅላላ ዋጋ 10,000/ አስር ሽ ብር/ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች የጫራታ ሃሳባቸዉን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥ ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጫራታ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ከሚያዚያ 13/2017 እስከ ሚያዚያ 27/2017 ዓ/ም 11፡30 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በ16 ተኛዉ ቀን በ28/2017 ዓ.ም 3፡00 ሠዓት ይታሸጋል በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨራታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በነጠላም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከፊት ለፈቱ መፈረም አለበት ።
- መ/ቤቱ ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በአል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት /በስልክ ቁጥር 05825400474/49 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት