ግልጽ የጫራታ ማስታወቂያ

0
78

በአብክመ የምስ/ጐጃም አስ/ዞን የእነማይ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽ/መሳሪያ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ዝርዝር መረጃውም በጨረታ ሰነዱ ተካቷል፡፡ በጨረታው ለመሣተፍ መሟላት የሚገባቸው፡-

  1. በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ አለባቸው፣
  2. የግዥው መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው አሸናፊ ላይ 2 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150/አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት እቃ ማለትም የጽ/መሳሪያ  ብር 10,000/አስር ሽህ ብር/ ብቻ  በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ፤በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ገንዘቡን በመ/ቤታችን መሂ-1 ገቢ ማደረግ አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን በኋላ ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት እ/ወ/ዐቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆኑ ነገሮች መኖር የለበትም ካለም ተጫራቹ ፖራፍ ማድርግ አለበት ፡፡ በጨረታ ሰነዱ እና በፖስታው ላይ የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  8. በባለሙያ የሚረጋገጡ እቃዎችን በባለሙያ እየተረጋገጡ የምንረከብ መሆኑ እና አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈባቸውን እቃዎች በእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስር ባሉ ንብረት ክፍል ድርስ አስፈላጊውን ወጭ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  9. አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅትኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ተጫራቾች የቀረቡትን የእቃ ዝርዝር ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጨረታ ውጭ/ውድቅ/ ይሆናሉ፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል፤ የጨረታ ማስከበሪውን ለየብቻ በማጠቃለያ ፖስታ በማሸግ እና በፖስታው ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ጽ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታ ይዘት ሳይቀይር ከጠቅላላ ዋጋው ላይ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ ዋጋ መሙላት ሲኖርበት በራሱ ዋጋ መሙያ ከሞላ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር ዐ586650100/ዐ586650008 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የእነማይ ወረዳ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here